ኢሳት የኢትዮጵያ ህዝብ ለዘመናት የተጠማውን መረጃ የወያኔን
አፈና ተቋቁሞ ለኢትዮጵያ ህዝብ ተደራሽነቱን አስመስክሮአል የኖርዌይ
የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ዕሑድ የካቲት 10 ቀን 2013 በደመቀ
ሁኔታ ተከብሯል አዳራሹን ሞልተው በጉጉት የጠበቁት የኖርዌይ ኢትዮጵያውያንም ተወዳጁ የኪነ ጥበብ ሰው ታማኝ በየነ ወደ አዳራሹ
ሲገባ በጋለ ስሜት ደማቅ አቀባበል አድርገውለታል የተለያዩ የእንኳን ደህና መጣህ ንግግሮች ተደርገዋል ።
ተወዳጁ የኪነ ጥበብ ሰው ታማኝ በየነ በሃገርና በህዝባችን
ላይ እየደረሰ ያለው የመብት ረገጣ አስመልክቶ በመረጃ የተደገፉ ትንታኔዎችን አቅርቧል።
በቀጣይ የጥበብ ሰው አርቲስት ታማኝ በየነ ወደ ዋናው የገቢ ማሰባሰቢያ የጨረታ መርሃ ግብር ተሸጋገረ ለጨረታ የቀረበው
የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ነበር ጨረታውን ለማሸነፍ የነበረው ፉክክር ሞቅ ያለ ነበር ሞቅ አድርጉት እያለ ሞቅ ባለ ዋጋ ባለ ዕድሉ
የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ በክብር ተረክበውታል ።
በአርቲስት እንዳለ እና በወጣቶች የተዝጋጀ የምርጫ 97 ድምፃችን ይመለስ በሚል ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተው የተገደሉ ወጣት
ሰላሚዊ ሰልፈኞችን ሁኔታ ያስታወስ ታሪካዊ ድራማ እና በየዝግጅቱ
ጣልቃ አዝናኝ ሙዚቃዎች ቀርቦአል ።
No comments:
Post a Comment